መዳኒት ሜዲካል ዳይሬክተሪ ከህክምና ጋር በተያያዘ ለማህበረሰቡ ሰፊ ግንዛቤን የሚፈጥር አዲስ የዲጂታል አገልግሎት ነው።
አገልግሎቱ በዋናነት አራት ነገሮች ላይ ትኩረት አድርጎ ከህክምና ጋር በተያያዙ ገዳዮች ግንዛቤን እንደሚፈጥር የአገልግሎቱ መስራች ባምላክ አለማየሁ ተናግረዋል።
በከተማችን አዲስ አበባም ሆነ በክልል ከተሞች ህክምና ለሚፈልጉ ሰዎች ጥራት ያለው እክምና የት እንደሚገኝ ይጠቁማል ።
ሌላው የትኛው ህክምና በየትኛው ዶክተር ይሰጣል ፤የትኛው ሆስፒታል ምን አይነት ህክምና እንደሚያድግ እና በህክምና ባለሞያዎች የታዘዙ መድኃኒቶች የት እንደሚገኙ ያሳያል ተብሏል ።
አገልግሎቱ በአማርኛ ፤በኦሮሚኛ ፤በትግረኛ እና በእግሊዝኛ ቋንቋዎች በመድሀኒት ዶት ኮም ዌብሳይት እና በቴሌግራም መገልገል ይቻላል ተብሏል ።
በሚቀጥለው ወር አገልግሎቱ ለደምበኞች በሚመች መልኩ በመተግበሪያ እና በአጭር የፅሁፍ መላኪያ መስመር አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገልጿል ።
በመሳይ ገ/ መድህን
ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም











