ሩስያ ላይ የተጣሉ ማእቀቦች የምግብ እና የግብርና ማዳበሪያን እንደማይመለከቱ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ::

የህብረቱ ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፍ ቦሬል እንዳስታወቁት፣ከሩስያ ጋር የትኛውንም አይነት የምግብ እና የግብርና ግብአቶችን የሚገበያይ አካል የሚጣልበት ማእቀብ የለም፡፡
በመሆኑም የዘርፉን ግብይት የሚፈፅሙ አካላት ያለምንም መሳቀቅ ይፋዊ ግብይትን ማድረግ ይችላሉ ብለዋል፡፡

የጣልናቸው የኢኮኖሚ ማእቀቦች ግባቸው የሩስያን ኢኮኖሚ ማዳከም እንጂ የዓለምን የምግብ እና ተያያዥ ችግሮችን ለማባባስ ያለሙ አይደሉም፣ መሰናክልም አይሆኑም ብለዋል ጆሴፍ ቦሬል፡፡

በመሆኑም ከምግብ እና ማዳበሪያ ጋር የተያያዙ ግዢዎች ያለ ድብብቆሽ በይፋ መዋዋል መገበያየት እንዲሁም ከሩስያ ወደቦች መጫን እና የገንዘብ ዝውውርን ማካሄድ ይችላሉ ነዉ ያሉት፡፡

የህብረቱ ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፍ ቦሬል በአለም አቀፍ ደረጃ ለተከሰተው የምግብ ቀውስ እና የዋጋ መናር የአውሮፓ ህብረት እና ማእቀቡን ተጠያቂ ማድረግ ፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ በበኩሏ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በሰጠቻቸዉ መግለጫዎች በዓሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለተከሰተዉ የኑሮ ዉድነትና ኢኮኖሚያዊ ጫና አሜሪካና ምዕራባዊያን የጧሏቸዉ ማዕቀቦች መሆናቸዉን ገልጻለች፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *