ወደ 939 ከሚደዉሉ ሰዎች መካከል ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት የሚጠይቁት የተሳሳተ መረጃ ነዉ ተባለ፡፡

መስመሩን አላግባብ የሚጠቀሙ ሰዎች መበራከት ለተቸገሩት በአፋጣኝ እንዳልደርስ እያደረገኝ ነዉ ብሏል፤የአዲስ አበባ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

ክፉዉን ያርቅና ድንገተኛ አደጋ ደርሶባችሁ ወይም አደጋ አይታችሁ ለሚመለከተው የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመር ኮሚሽን ስትደውሉ ስልኩ ላይሰራ ወይም በተደጋጋሚ ተይዟል ሊላችሁ ይችላል፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳለዉ
በአብዛኛዉ ይህ የሚሆነዉ ችግር ያልገጠመናቸዉ ሰዎች መስመሩን እየያዙት ነዉ ብሏል፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ሚሽን አደጋ ለመከላከል አጭር የስልክ ጥሪ መስመር ለተገልጋዮቹ 939 ማስቀመጡ ይታወሳል፡፡
ወደ ጥሪ ማእከሉ ከሚደወሉ ጥሪዎች መካከል 90 በመቶ የሚሆኑት ደዋዮች የጥሪ ማዕከሉን ለመጨናነው እና ለቀልድ የሚደዉሉ መሆናቸዉን ከኮሚሽ ሰምተናል፡፡

አንዳንድ ደዋዮች ትዳር ፈልጌ ነው፣ የስነልቦና አማካሪ እፍልጋለሁ፣ ፖሊስ ጣበያ ነው ውይ? የሚሉ እና ሌሎችንም አላስፈላጊ ጥያቄዎች በማቅረብ መሰመሩን እንደሚያጨናንቁት ኮሚሽኑ አስታዉቋል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኘነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ አደጋ ለመከላከል የተዘጋጀው የስልክ መሰመር በቀላጆች እየተጨናነቀ ይገኛል፡፡

በዚህም አደጋ በመከላከሉ እረገድ እክል እየፈጠረ ይገኛል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ እየሰራን እንገኛለን ያሉት አቶ ንጋቱ በቅርቡም በጂፒኤስ የታገዘ አሰራር ለመተግብር የሚያስችል አዲስ አሰራር ይዘን እንመጣለን ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *