አፍጋኒስታን ባጋጠማት የመሬት መንቀጥቀጥ ከአንድ ሺህ በላይ ዜጎቿን አጥታለች፡፡

ከ6 ነጥብ 1 ሬክተር ስኬል በላይ የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ በሰሜናዊ አፍጋን እና ፓኪስታን የሚገኙ ተራራማ አካባቢዎችን አጥቅቷል፡፡

ከ600 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባለ ሲሆን ተጎጂዎችን የማዳን እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ የታሊባን አደጋ ጊዜ ባለሙያዎች አስታውቀዋል፡፡

አደጋው የተከሰተው ገጠራማ አካባቢዎች ላይ በመሆኑ ፈጣን እርዳታ ለማድረስ ፈተና ገጥሞት እንደነበርም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

የታሊባን አየር ሃይል ተጎጂዎችን ለመርዳት እና አስፈላጊ ድጋፎችን ለማቅረብ ግዳጅ ላይ እንደሚገኝም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *