ፏን ኋን የሲሚንቶ ምርት ጥቅም ላይ እንዳይውል ታገደ::

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፏን ኋን የሲሚንቶ ምርት ጥቅም ላይ እንዳይውል ማገዱን አስታዉቋል፡፡
ህብረተሰቡ ፏን ኋን የሲሚንቶ ምርት ጥቅም ላይ እንዳይውል የታገደ መሆኑን ተረድቶ እንዳይጠቀም ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ፏን ኋን የሲሚንቶ ጥቀም ላይ እንዳይዉል የታገደዉ የሚጠበቅበትን የጥራት ደረጃ መስፈርት ባለሟሟላቱ እንደሆነም ታዉቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ድርጅቱ የሚጠበቅብትን መስፈርት እንዲያሟላ ተደጋጋሚ የመስጠንቀቂያ ደብዳቤ መጻፉን የገለፀዉ ሚኒስቴሩ ባለማስተካከሉ እርምጃዉን እንደወሰደ አብራርቷል፡፡

ፏን ኋን ሲሚንቶ አሁን ላይ ወደ ገበያ ያሰራጨዉን ምርት በራሱ ወጪ እንዲሰበስብ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል፡፡

በአባቱ መረቀ

ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *