አዋሽ ባንክ ለሼባ ማይልስ አገልግሎት የሚመዘገቡ ደንበኞቹን ሊሸልም ነው ።

አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር የሼባ ማይልስ ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞቹን ለአገልግሎቱ በመመዝገባቸው ሊሸልማቸው መሆኑ ተነግሯል ።

አዋሽ ባንክ በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር አዋሽ ሼባ ማይልስን በይፋ ስራ የማስጀመር እና የአጋርነት ስምምነት ተፈራርሟል ።

በሁለቱ ተቋማት መካከል የተፈረመው ይህ ስምምነት የአዋሽ ባንክ አካውንት ያለው እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ አባል የሆነ ማንኛውም ግለሰብ ካርዱን አውጥቶ መጠቀም የሚያስችል መሆኑን የአዋሽ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ከፍያለው ሽፈራው ተናግረዋል ።

ደንበኞች በሼባ ማይልስ በመጠቀም ግዥ ሲፈፅሙ የሚሸለሙ ሲሆን ፣ ለአገልግሎቱ በመመዝገባቸው ደግሞ 200 ማይልስ የሚሸለሙ ይሆናል ።

በካርዱ በATM ማሽኖች ፣ በባንኩ ወኪሎች እና በተለያዩ ማዕከላት ገንዘብ ማውጣት እና መጠቀም ይችላሉ ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአለምአቀፍ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ይልማ ጎሹ እንደገለፁት የሼባ ማይልስ ካርድ ተጠቃሚ የሆነ ደንበኛ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጨማሪ በስታር አሊያንስ ስር ባሉ 27 አየር መንገዶች ላይ መጠቀም ይችላል።

ሼባ ማይልስ የሰማያዊ ፣ ብር ፣ ወርቅ እና ፕላቲኒየም ደረጃዎች ያሉት ሲሆን እንደ ካርዶቹ ደረጃ በአውሮፕላን ጣቢያዎች ቅድሚያ የማግኘት ፣ ትርፍ ሻንጣ ቢኖራቸው ያለተጨማሪ ክፍያ ማሳለፍ ፣ በማይልሱ ብዛት የመቀመጫ ቦታዎችን ጭምር የመቀየር አቅም እንዳለውም አክለው ገልፀዋል ።

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *