ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድቡ ጋር ተያይዞ የአውሮፓ ህብረት ያወጣውን መግለጫ አወገዘች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ከሰሞኑ የአውሮፓ ህብረት ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተገናኘ ያወጣው መግለጫ ለግብፅ ያደላ እና ተቀባይነት የለውም ብለዋል ።

ተሰናባቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ሲሆኑ በዚህ ወቅት እንዳሉት የአውሮፓ ህብረት የሰጠው ለግብፅ ያደላ በመሆኑ አቋሙን እንዲያስተካክል ጠይቀዋል ።

ኢትዮጵያ የታችኛው ተፋሰስ አገራትን የመጉዳት ፋላጎት እንደሌላት የገለፁት አምባሳደሩ፣ህብረቱ ይህን እውነታ ያላገናዘበ መግለጫ ሰጥቷል ።

የአውሮፓ ህብረትና ግብፅ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ከሰሞኑ በሉግዘንበርግ ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያ አሳሪ ስምምነት እንድትፈርም መጠየቁ የሚታወስ ነው።

በተለይም ህብረቱ የግብፅን የውሃ ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፁ አነጋጋሪ ሆኗል።

በአባቱ መረቀ

ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *