ኢትዮጵያ የልጆቿን ደም በየጊዜው የምትጠጣ መሆን የለባትም ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሀገሪቱ አሁናዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ባደረጉት ንግግር፣ የሰላም እጦት ብዙዎችን አሳጥቶናል፣ የጭካኔ ጥግ እንድናይ አድርጎናል ብለዋል፡፡
የሰላም ጉዳይ ጦርነት ስላበቃ ብቻ ማውራት የለብንም፣ ሰላም ባለበት ወቅትም ቢሆን መነጋገር ይገባናል ነዉ ያሉት ፕሬዝዳንቷ፡፡

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ ላይ የተፈጠረው ክስተት መሆን የሌለበት እና መፈጠር የሌለበት ጉዳይ ነበር ብለዋል፡፡
የሰላም እጦት እርስ በርሳቸውን እንዳንተማመን አድርጎናል፣ አፋጅቶናል ከዛ በላይ ደግሞ ሀገሪቷን ትልቅ ዋጋ አስክፍሏታል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ግዚያት በተከሰቱ ጥቃቶች የተነሳም ህጻናት፣ ሴቶች እና አረጋዊያን የጥቃቱ ዋነኛ ሰለባ መሆናቸውንም ነው ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተናገሩት፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ እና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ፣ የተደፈሩ ሴቶች አደባባይ ወጥተው ሰቆቃቸውን የተናገሩበት አጋጣሚ ተፈጥሯል፣ ይህ ደግሞ የሚያሳየው ጥቃቱ ምን ያህል አስከፊ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ ግጭት በተከሰተባቸው ቦታዎች ተዘዋውረው መጎብኝታቸውን ገልጸዉ፣ በአብዛኛው በሁሉም አካባቢዎች ሴቶች እና ህጻናት ሰው ሰራሽ በሆኑ ጥቃቶች ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *