አንድ መቶ የሚሆኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚሳተፉበት ኤግዚቢሽን ከሰኔ 23 እስከ ሰኔ 25 ይካሄዳል፡፡

በመድረኩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ስራቸውን የሚያስተዋውቁ ሲሆን የውይይት መርሃግብርም እንደተያዘለት የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይርክተር አቶ ሄኖክ መለሰ ተናግረዋል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንትን ማክበር አንድም የዘርፉን የገጽታ ግንባታ እንቅስቃሴን የበለጠ ለማጉላት፤ በሌላ በኩል ደግሞ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር ይረዳል” ያሉት ደግሞ፤ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ሄኖክ መለሰ ናቸው።
ከውይይቶቹም መካከል በሃገራችን እየታየ ባለዉ የፕለቲካ ቀውስ፣ ስራ አጥነት እና ከስርአተ ፆታ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እንደሚነሱበት ተጠቁሟል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደተናገሩት፣ ከዚህ በፊት የነበረው የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጁ አሳሪ ነበር።

ነገር ግን አዋጁ ዛሬ ላይ ማሻሻያ ስለተደረገበት ድርጅቱ ከመቼም ጊዜ በላይ ይህን ተጠቅመው በሃገሪቱ የሰላም እና የልማት ስራዎች ላይ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ኹለተኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንትም “ንቁ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለሰላም ለዲሞክራሲና ለልማት” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ሰምተናል፡፡
በኢትዮጵያ በቁጥር 4 ሺህ የሚደርሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዳሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *