የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በእለቱ በመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ ከተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከልም፡-

የሰላምና የደህንነት ሁኔታዎችን በተመለከተ፤- በሃገሪቱ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችና የሰላም እጦቶችን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት መንግስት ህግን የማስከበር የተቀናጀ እርምጃን በሁሉም አካባቢዎች አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በእነዚህ እርምጃዎች የመንግስት የፀጥታ አካላት የሽብር ብድኖችን አባላት በመደምሰስና በማደን ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በተመለከተ ፡- በኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ላይ ልዩ ልዩ አሻጥር በመፍጠር ዜጎች እንዲማረሩ እያደረጉ ያሉ ስግብስግ ግለሰቦች፣ ከእኩይ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰቷል፡፡

የሰሜኑን ጦርነት በተመለከተ ፤- የኢትዮጲያ መንግስት ለሰላም መንገድ ሲከፍት ከነሙሉ ብቃቱና ፍላጎት ነው፣ ነገር ግን ይህንን እድል መጠቀም ያለመጠቀም የሌላኛው ወገን ውሳኔ ይሆናል፡፡

የእርዳታ አቅርቦቱን በተመለከተ ፤- በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ በተሳለጠ መልኩ እንዲዳረስ የኢትዮጵያ መንግስት እየሰራ ነው፡፡ የተለያዩ አካባቢዎች በህወሃት ቢያዙም ሰብአዊ ድጋፍ ያለማቋረጥ ቀጥሏል፡፡

የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ ፤- የህዳሴ ግድቡ በተያዘው የጊዜ ገደብ እንዳይሞላ የተለያዩ አጀንዳዎች ሲፈጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ይህ ግብግብ የመንግስትን አቅጣጫ ለመቀየርና ግድቡ በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ የሚደረግ ጥረት ነው፤ ይህ እቅዳቸዉ ግን መቼም አይሳካም ብሏል፡፡

በየዉልሰዉ ገዝሙ
ሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.