200 የሚጠጉ አዉቶብሶች የድጋፍ ሰጭነት ዉላቸዉ መቋረጡን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ውል ለተጨማሪ 6 ወራት የተራዘመው 180 ለሚደርሱት ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

ውሉ ከመጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 2 ቀን 2015 ዓ.ም መራዘሙ የተገለጸ ሲሆን ውል የተራዘመላቸውም 380 ከሚጠጉ አውቶብሶች 180 የሚሆኑት ብቻ መሆናቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ከጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ 380 የሚሆኑ ሀገር አቋራጭ አውቶብሶች በኪራይ መልክ በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ180 የሚጠጉት ውል ሲራዘም የቀሪዎቹ በተለያየ ምክንያት በራሳቸው ፈቃድ ውላቸውን ያቋረጡ መሆናቸዉን የአዲስ አበባ ትራንፖርት ቢሮ የኮሚውኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ እፀገነት አበበ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
በዚህም ምክንያት በህብረተሰቡ ላይ የትራንስፖርት መስተጓጎል እና እጥረት እንዳይከሰት አሊያንስን ጨምሮ ሌሎች አውቶብሶች አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚደረግ ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *