አርሰናል የጄሱስን ዝውውር አጠናቀቀ::

አርሰናል ጋብሪኤል ጄሱስን በ45 ሚ.ፓ የዝውውር ክፍያ ከማንቸስተር ሲቲ አዘዋውሯል ፡፡ ብራዚላዊው ከመድፈኞቹ ጋር የረዥም ጊዜ ኮንትራት ተፈራርሟል ፡፡

የ25 ዓመቱ ተጫዋች ሚኬል አርቴታ በዚህ ክረምት ያስፈረመው አራተኛ ተጫዋች ሆኗል ፡፡ አማካዩ ፋቢዮ ቪዬራ ፣ ግብ ጠባቂው ማት ተርነር እና አጥቂው ማርኪኒሆስ ቀደም ብለው ቡድኑን ተቀላቅለዋል ፡፡

አርቴታ በጄሱስ መፈረም ‹‹መደሰቱን›› ተናግሯል ፡፡ ‹‹ክለቡ እንደ እርሱ ዓይነት ትልቅ ተጫዋች ለማስፈረም ከፍተኛ ጥረት አድርጎ ተሳክቶለታል ›› ብሏል ፡፡

በአቤል ጀቤሳ
ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *