ኢኮዋስ በማሊ ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ አነሳ፡፡

ኢኮዋስ በማሊ ጥሎት የነበረው ማዕቀብ መፈንቅለ መንግስቱን ያካሄዱ አካላት ላይ የፋይናንስ እና የጉዞ እገዳን ያካተተ ነበር፡፡
በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ማሊ ከተደረገው መፍንቅለ መንግስት ጋር በተያያዘ ለተፈጠረው አለመረጋጋት ዋነኛ ምክንያቱ መፈንቅለ መንግስቱን ያካሄዱ ሰዎች ናቸው በሚል ነበር ኢኮዋስ ማዕቀብ ጥሎ የነበረው፡፡

የማሊ ጁንታ ከሁለት ዓመት በፊት በምርጫ አሸንፈው የአገሪቱ ፕሬዘዳንት የነበሩት አቡበከር ኬታን በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን መቆጣጠሩ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ ላለፉት ሁለት አመታት በሀገሪቱ ከፍተኛ የስላም እጦት ነግሶ ቆይቷል፡፡

የቀጠናው ሰላም አሳሳቢ እየሆነ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ፣ ኢኮዋስ በተደጋጋሚ ለማሊ ማስጠንቀቂያ ሲስጥ ነበር፡፡
አሁን ባሉት መረጃዎች መሰረት በ40 ዓመቱ ኮለኔል አስሚ ጎይታ የሚመራው የማሊ ጁንታ ወታደራዊ መንግስት፣ ምርጫ ለማድረግ እና ስልጣን በህዝብ ለተመረጠ መንግስት ለማስረከብ አምስት ዓመት ከስድስት ወር ያስፈልገኛል ብሏል።

የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህብረሰብ በምህጻሩ ኢኮዋስ ከዚህ በፊት ባደረገው የመሪዎች ጉባኤ ስልጣን በሀይል የተቆጣጠረው የማሊ ጁንታ ምርጫ የሚያካሂድበትን እቅድ እንዲያሳውቅ ጠይቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.