የብሩል ትሬዲንግ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ እንቁጣጣሽ ሃይሌ፤ ድርጅቱ በሃገሪቱ የሚታየውን የውጪ ምንዛሬ እጥረት በመቅረፍ እና የስራ እድል በመፍጠር የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
ብሩል ትሬዲንግ በውክልናው ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራት በሚያቀርበው የፈርኒቸር እቃዎች ክፍያን የሚቀበለው በዶላር በመሆኑ ለሃገራችን ትልቅ ሚና እንዳለዉ ተናግረዋል፡፡
ድርጅቱ ይህን ያለዉ በዛሬዉ እለት የፊልም እና የማስታወቂያ ባለሙያዋን አርቲስት ሃናን ታሪክን አምባሳደር ማደረጉን ባሳወቀበት መድረክ ላይ ነዉ፡፡
ድርጅቱ ላለፋት 6 አመታት ከቱርክ ኩባንያ ጋር የምስራቅ አፍሪካ ወኪል በመሆን ቅንጡ እና ደረጃቸውን የጠበቁ የፈርኒቸር እቃዎችን በማምጣትና ከሌሎች ሃገራት ጋር በዉክልና መልክ ሲሰራ መቆየቱንም ዋና ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል፡፡
በመሳይ ገ/መድህን
ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ.ም











