ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን የንግድ ትርኢት ልታስተናግድ ነው።

በአለም አቀፍ የኮንስትራክሽን የንግድ ትርኢት አካል የሆነውን the big 5 construct Ethiopia፣ ሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ልታዘጋጅ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል።
የንግድ ትርኢቱም ከግንቦት10 እስከ 12/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳልም ተብሏል።

በዝግጅቱም ላይም ከ 100 በላይ የሚሆኑ አለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ምርቶች፣ አገልግሎት ሰጪ እና የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን እንዲሁም ሀገር በቀል ቁልፍ ተቋማትን ይዘዉ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡

ከጣልያን፣ ቱርክ ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፣ ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ ከ15 በላይ ከሚሆኑ ሀገራት የተዉጣጡ ተሳታፊዎች እንደሚገኙበት የኹነቱ አዘጋጅ የሆኑት “ኢቴል ኢቨንትስ” እና “ዲኤምጂ ኢቨንትስ” በዛሬው እለት በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡

ስድስት ሺህ የሚሆኑ የሀገር ውስጥ ገዢዎች ይሳተፉበታል የተባለ ሲሆን ከገዢዎቹ መካከል መሀንዲሶች፣ የፕሮጀክት ስራ አስኪያጆች፣ አርክቴክቶች፣ የጥራት ተቆጣጣሪዎች፣ አከፋፋዮች እና አምራቾች ይካተታሉ ተብሏል።

በኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ ሪፖርት መሰረት ዘርፉ ባለፉት 5 አመታት በአማካኝ የ11 በመቶ እድገት አሳይቷል።
የኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ በማእከላዊ ስታስቲክስ ገለጻ መሰረት ከኢትዮጵያ የሰራተኛ ኀይል ውስጥ 5 በመቶ የሚሆነውን ይይዛል።

በረድኤት ገበየሁ
ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *