ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች በጥቂቱ:-

  1. በዜጎች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ ይከለከላል፤ ለሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ዜጎች ላይም ጥቃት ተፈጽሟል፤ ለምን?
  2. ባለፉት አራት አመታት በዜጎች ላይ በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት ብሄራዊ ስጋት አይደለም ወይ? በዚህ ድርጊት የተሳተፉት ላይ ለምን እርምጃ አልተወሰደም?
  3. ከትህነግ ጋር ለመወያየት ሰው መመደቡን ሰምተናል፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቡድኑን ሽብርተኝነት ስያሜ ባላነሳበት ሁኔታ መደራደር ወንጀል አይደለም ወይ?
  4. የክልል መንግስታት በክልላቸው የሚኖሩ ዜጎችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ካልቻሉ ለምን አይጠየቁም?

የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሽ እየሰጡ ሲሆን እስካሁን ካነሷቸዉ ሃሳቦች መካከል ንጹኃንን በጅምላ መግደል የፖለቲካ አላማን የሚያሳካ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሽብር ቡድኖች የሚያደርሱትን ጥቃት እና በደል ከማንነት ጋር ማያያዝ አይገባም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
መንግስት የህዝብን ደህንነት እና ሰላም ማረጋገጥ ዋነኛ ስራው ቢሆንም ህዝቡም መንግስትን ማዳመጥ ይኖርበታል ብለዋል፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ ሁሉም ባለው እውቀት እና ግንዛቤ ከማውራት እና ከመተቸት ውጪ መንግስትን በአግባቡ እያዳመጠ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *