በአዲስ አበባ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከስድስት ጊዜ በላይ የሽብር ተግባር ከሽፏል—ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ

በመድናዋ በአንድ ሳምንት ብቻ ሊፈፀም የነበረ ስድስት የሽብር እንቅስቃሴ ማክሸፉን መንግስት አስታዉቋል፡፡

በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልም የሽብር ጥቃት ለመፈፀም እንቅስቃሴ ሲደረግ መንግስት እንደደረሰበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል፡፡

እያጠቃን ያለው አካል የተለየ መልክ ያለው ሰው ሳይሆን እኛን የሚመስል ሰው ነው ሲሉ ገልፀውታል፡፡
በሃገራችን ህግና ስርዓትን ለማስጠበቅ ለእያንዳንዱ ዜጋ አንዳንድ ወታደር ማስቀመት አንችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይልቅ ተሰናስሎ በጋራ ሃገርን መጠበቅ ይበጃል ብለዋል፡፡

የፀጥታ አካላት ብቻ ሳይሆን ሃገርን የሚጠብቅ ዜጋም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በየዉልሰዉ ገዝሙ
ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *