በአዲስ አበባ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
የቢሮው ሃላፊ አቶ ዳዊት የሺጥላ እንዳሉት በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የአዉቶብስም፣ የታክሲም የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል፡፡

የማሻሻያ ዋጋዉም የታክሲ ትንሹ የ 50 ሳንቲም ጭማሪ ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ የ2 ብር ጭማሪ ለማድረግ መዘጋጀቱን ቢሮው አስታውቋል፡፡
በነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሪ ከተደረገ ወዲህ በተለይም ታክሲዎች በራሳቸዉ ታሪፍ እየጨመሩ ከተሳፋሪዎች ጋር አላስፈላጊ እስጠገባ ዉስጥ ሲገቡ ይስተዋላል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.