“ግሪን ቴክ አፍሪካ” በተሰኘ ኩባንያ የተመረቱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዛሬ ስራ ጀምረዋል፡፡

ተሸከርካሪዎችን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በዛሬዉ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ አስጀምረዋል።

የትራንስፓርት ዘርፉን ተደራሽና ፈጣን በማድረግ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የትራንስፖርት ስርዓት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በዚህ ወቅት ተናግረዋል፡፡

ስራ የጀመሩት ተሽከርካሪዎች ለመዲናዋ ነዋሪዎች ለአንድ ወር ያህል ነጻ የትራስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጡ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ተሽከርካሪዎቹ የተለያየ መጠን ያላቸውና የአየር ብክለትን በመቀነስ ለአካባቢ ጥበቃና ደህንነት ጉልህ ሚና አላቸው ነው የተባለው፡፡

በግሪን ቴክ አፍሪካ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች በአንድ ሙሉ ቻርጅ በአማካይ ከ200 እስከ 240 ኪሜ ሊጓዙ የሚችሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ ርቀት በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች 20 ብር ወጪ እንደሚጠይቅና በነዳጅ በሚሠሩ ተሽከርካሪዎች አሁናዊ ዋጋ እስከ 950 ብር የሚጠይቅ መሆኑን በንፅፅር ገልፀዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *