ባንኩ መርሃ-ግብሩን ላለፉት አምስት ወራት ሲያካሂድ መቆየቱን ያስታወቀ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ባለእድለኞች ሽልማታቸውን በዛሬው እለት አስረክቧል፡፡
2ተኛው ዙር የሕብረት ባንክ የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ እና ይሸለሙ” መርሃ ግብር የሎተሪ ዕጣ ሰኔ 02/ 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ ዕድል አዳራሽ መውጣቱ የሚታወስ ሲሆን፣ የአውቶሞቢል ባለእድለኛው የሎተሪ ቁጥር 14-11-12-25 ሆኖ ወጥቶ እንደነበርም ይታወሳል፡፡
ባለእድለኛው አባ ኪዳነ ማርያም ሽልማታቸውን ከባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ ተረክበዋል፡፡
አቶ መላኩ የመርሃግብሩ መኖር ለባንኩ ደንበኞች የቁጠባ ባህል መዳበር እና የውጭ ምንዛሬን በህጋዊ መንገድ መመንዘርን ያበረታታ ነው ብለዋል፡፡
ባንኩ አሁን ላይ ከ420 በላይ ቅርጫፎችን ከፍቶ እያገለገለ ይገኛል ያሉት አቶ መላኩ፣ የሃብት መጠኑም 70 ቢሊየን ብር ድርሷል ብለዋል፡፡
ባንኩ ዛሬ ባወጣው እጣ የሱዙኪ ዲዛዬር የተሸከርካሪ ሽልማትን ጨምሮ በእጣው ባልሶስት እግር ተሽከርካሪ፣ ቴሌቪዥን ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ ማቀዝቀዣ እና የውሃ ማጣሪያ ማሽኖችን ለባለ እድለኞች አስረክቧል፡፡
ህብረት ባንክ ሰኔ 24 ቀን በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ የሽልማት እጣ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
በአብዱሰላም አንሳር
ሐምሌ 07 ቀን 2014 ዓ.ም











