በመዲናዋ ሊተገበሩ የታሰቡ የከተማ ፈጣን አዉቶቢስ ትራንስፖርት ኮሪዶሮች ይፋ ተደረጉ

በአዲስ አበባ ከተማ ሊተገበሩ የታሰቡ የከተማ ፈጣን አዉቶቢስ ትራንስፖርት (Bus Rapid Transit) ኮሪዶሮችን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ይፋ አድርጓል።

የከተማ ፈጣን አዉቶቢስ ትራንስፖርት (BRT) በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች እየተተገበረ ያለ ዘመናዊ የትራንስፖርት ሲስተም ሲሆን፤ ራሱን የቻለ የተከለለ መንገድ፣ በቀላሉ የተሳፋሪን ፍሰት ማስተናገድ የሚያስችሉ መጠበቂያዎች፣ ከአዉቶቢስ ዉጭ የሆነ የክፍያ ሥርዓት፣ ለአዉቶቢስ ጥገናና ስምሪት የሚያገልግል ዴፓ ያለው፣ በመንገድ መጋጠሚያዎች ለአዉቶቡስ ቅድሚያ የሚሰጥ እና የኮሪዶር ልማትን የሚያበረታታ የብዙሃን ትራንስፖርት ዓይነት ነዉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የብዙሃን የትራንስፖርት ችግር በመፍታት ፈጣን፣ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ተደራሽ፣ ወጪ ቆጣቢ እና አካባቢያዊ ተስማሚነቱ የተረጋገጠ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎትና ሥርዓት እንዲኖር ታስቦ 15 የBRT ኮሪደሮች ተለይተዉ በመሪ እቅዱ ላይ መቀመጡን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት ፈጣን የአውቶቢስ ትራንስፖርት አገልግሎት መሥመሮች እንደሚከተከለው ተለይተዋል፦

መሥመር-1፡- ከዊንጌት ተነስቶ በሆላንድ ኤምባሲ 3 ቁጥር ማዞሪያ አድርጎ አለርት አየር ጤና

መሥመር-2፡- ከዊንጌት በመርካቶ አድርጎ ሜክሲኮ- ጎፋ ወደ ጀሞ የሚደርስ

መሥመር-3፡- ከጉለሌ በለገሃር ጎፋ ገብርኤል አድርጎ ላፍቶ ሃና ማርያም የሚሄድ

መሥመር-4፡- ሽሮሜዳ በአራት ኪሎ በመገናኛ አድርጎ ኮተቤ ካራሎ የሚወስድ

መሥመር-5፡- ከመገናኛ በቦሌ ድልድይ አድርጎ ለገሃር

መሥመር-6፡- ከጦር ኃይሎች በቄራ አድርጎ ቦሌ ድልድይ

መሥመር-7፡- ከአየር ጤና በቶታል አድርጎ ብስራተ ገብርኤል በፑሽኪን አደባባይ ሜክሲኮ

መሥመር-8፡- ከቦሌ በኡራኤል ካዛንቺስ በአራት ኪሎ አድርጎ ስድስት ኪሎ ፈረንሳይ የሚያደርስ

መሥመር-9፡- ከአየር ጤና በመካኒሳ ቆጣሪ እስከ ቃሊቲ

መሥመር-10፡- ከቃሊቲ ቦሌ

መሥመር-11፡- ከካራሎ በሲኤምሲ ሰሚት አድርጎ በቦሌ ለሚ አይቲ ፓርክ የካ ቦሌ አራብሳ እስከ አያት

መሥመር-13፡- ከቡልቡላ በቂሊንጦ ኮዬ ፈጬ

መሥመር-14፡- ከለቡ በአቃቂ ኮዬ ፈጬ

መሥመር-15፡- ከኢምፔሪያል ሆቴል ጎሮ አድርጎ ቦሌ አራብሳ

መሆናቸዉን ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ አመላክቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 07 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *