የተማሪ ቢንያም ኢሳያስን ትምህርት በተመለከተ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የሕክምና ት/ቤት ለተማሪው የትምህርት ሂደት ይረዳሉ ያሏቸውን አማራጮች ማቅረባቸው ይታወሳል።
ሆኖም ተማሪ ቢንያም ብቸኛ ፍላጎቱ የሕክምና ትምህርትን መማር እንደሆነ ገልጿል።
በዚሁም መሠረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ኮሚሽን በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ የሕክምና ትምህርቱን እንዲቀጥል ተወስኗል።

እስካሁን የተቋረጡ ትምህርቶችንም በማካካስ ትምህርቱን ካቆመበት እንዲቀጥል ይደረጋል ብሏል ዩኒቨርሲቲው።
ምንም እንኳን የትምህርት ሂደቱ ከባድ እና ውስብስብ ቢሆንም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የሕክምና ት/ቤቱ የተማሪ ቢንያምን ትምህርት የተሳካ እንዲሆን የሚችሉትን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተገልጿል።
ኢትዮ ኤፍ ኤን 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 08 ቀን 2014 ዓ.ም











