በአዲስ አበባ 96 ቦታዎች የእሁድ ገበያ ተቋቁመዋል ተባለ፡፡

“በሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራት፣ የሰብልና የአትክልት አቅራቢዎች፤ የጅምላ ነጋዴዎችና በምግብ ማቀነባበርያ የተሰማሩ ፋብሪካዎች እንዲሁም በኦሮምያ ልዩ ዞን የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራትን በማሳተፍ በየሳምንቱ የእሁድ ገበያ በከተማዋ በተመረጡ 96 ቦታዎች የፍጆታ እቃዎች እየቀረቡ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የእሁድ ገበያው በአምራችና በሸማቹ መሀከል የነበረውን የገበያ ሰንሰለት በመበጣጠስ፤ተጠቃሚው በቀጥታ ከአምራቾች ምርትን በወቅቱና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ በማድረግ የኑሮ ውድነት ጫናው ዝቅተኛ ገቢ ያለውን የማህበረሰብ ክፍል እንዳይጎዳ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

በእነዚህ በተመረጡ የእሁድ ገበያዎች የሚቀርቡ የፍጆታ እቃዎች የዋጋቸዉን ተመጣጣኝነትና አቅረቦትን በተመለከተ አድማጮች አስተያየቶቻችሁን ልትሰጡበት ትችላላችሁ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 12 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *