የሩሲያና የቱርክ መሪዎች ኢራን ገብተዋል፡፡

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲንና የቱርኩ አቻቸዉ ረሲጵ ጣይጵ ኤርዶሃን ወደ ኢራን ገብተዋል፡፡

መሪዎቹ በቴህራን በሚኖራቸዉ ቆይታ ከፕሬዝዳንት ኢብራሂም ሬሲ ጋር በሶስትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተለይም ፑቲንና ኤርዶሃን ዩክሬን በጥቁር ባህር በኩል ስንዴን ለአለም ገበያ እንድታቀርብ በሚቻልበት ሁኔት እንደሚመክሩ አልጄዚራ አስነብቧል፡፡

በተጨማሪም ሶስቱ መሪዎች በኢራን የኒኩለር ዉዝግብና በሶሪያ ጉዳይ እንደሚመክሩም ይጠበቃል፡፡

ኢራን በአሜሪካና አጋሮቿ የሚደርስባትን ተጽዕኖ ለመቋቋም ከሩሲያና አጋሮቿ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ጥረት እያደረገች ትገኛለች፡፡

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 12 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.