የኢራኑ ናሽናል እና የሩሲያዉ ጋዝ ፕሮም ታሪካዊ ነዉ ያሉትን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኢራን ናሽናል ነዳጅ ኩባንያ እና የሩሲያዉ ነዳጅ አምራች ጋዝ ፕሮም ወደ 40 ቢሊዮን የሚጠጋ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸዉን የኢራን የነዳጅ ሚኒስቴር ዜና ወኪል ሻና ዘግቧል፡፡
የኢራን ባለስልጣናት እንደገለጹት 20 ሚሊዮኑ ለኪሽ እና ለሰሜናዊ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ የሚከፋፈል ሲሆን፤በቀን የ100 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ተጨማሪ ጋዝ እንዲያመርቱም ይረዳል ነዉ የተባለዉ፡፡

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከኢራኑ አቻቸዉ ጋር ለመምከር ወደ ቴህራን ባቀኑበት ወቅት የሁለቱም ኩባንያ ሃላፊዎች በኦንላይን ባደረጉት ዝግጅት ነዉ ስምምነቱ የተፈረመዉ፡፡
ጋዝ ፕሮም የኢራን ናሽናል ነዳጅ ኩባንያን የኪሽ እና ሰሜናዊ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ ቦታዎችን በማልማት ረገድ እንደሚደግፋት እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ስድስት የጋዝ ማምረቻ ቦታዎችን በማልማትም ትብብር እንደሚያደርግ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ጋዝ ፕሮም ከዚህ በተጨማሪም የተፈጥሮ ጋዝ አምራች ፕሮጀክትን እና የጋዝ ማስተላለፊያ ቱቦዎችን በመገንባት ኢራንን እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡

ኢራን ከሩሲያ በመቀጠል በዓለም ሁለተኛዋ ከፍተኛ የጋዝ ክምችት ያላት ሀገር ብትሆንም፣ የአሜሪካ ማዕቀብ ከቴክኖሎጂ ጋር ግንኙነት እንዳይኖራት ያቀባት በመሆኑ ወደ ዉጭ የሚላከዉ የጋዝ ዕድገት አዝጋሚ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
የሩሲያ-ዩክሬንን መዉረር በዓለም ነዳጅ እና የነዳጅ ገበያዉ ላይ ባሳደረዉ ተጽዕኖ ምክንያት የፑቲን የቴህራን ጉብኝት በከፍተኛ ሁኔታ የዓለምን ትኩረት የሳበ እንደሆነ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *