በሀገራችን ከ40 በመቶ በላይ የሞት ምጣኔ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚከሰት ነዉ ተባለ፡፡

በሀገራችን ካለው የሞት ምጣኔ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚከሰት ሞት መሆኑ ተገልጿል።

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር፣ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እያደረሱ ያሉት ጉዳት በሚል ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

የማህበሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ጌትነት እንደተናገሩት፣ በሀገራችን ከሚከሰት ሞት ውስጥ 40 በመቶው የሚከሰተው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ነው።

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በሀገራችን ስር እየሰደዱ እንደሚገኙ ያነሱት ምክትል ዳይሬክተሩ ለዚህ ጉዳይ መባባስ ብዙ ምክንያቶች እንዳሉ ያነሳሉ።

አሁናዊው በሀገራችን ያለው የአመጋገብ ስርዓት አንዱ መሆኑን ያነሱት አቶ አክሊሉ፣ በይበልጥ በወጣቱ ዘንድ የተለመደው በፋብሪካ የተቀነባበሩ የታሸጉ ምግቦችን መመገብ ሲሆን፣ ይህም ተላላፊ ላልሆኑ የበሽታ አይነቶች ተጋላጭነታቸው እንደሚጨምር እንደሚያደርግ አንስተዋል።

ሌላው እና ዋናው ምክንያት ነው ተብሎ የሚነሳው ደግሞ ትምባሆ ማጨስ ፣አልኮል መጠቀም እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ ናቸው።

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተብለው የሚጠቀሱት የልብ ህመም ፣ካንሰር ፣የመተንፈሻ አካላት ህመም ፣የደም ግፊት እንዲሁም የስኳር ህመም ናቸው ።
በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው የሞት ምጣኔ 71 በመቶው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ሲከሰት ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአመት በአለም 41 ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ ተብሏል።

በእስከዳር ግርማ

ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.