የዩክሬን ቀዳማዊት እመቤት ኦሌና ዜኔኒስካ የአሜሪካ ኮንገረስን አጥብቀው መማጸናቸው ተነግሯል፡፡
ኦሌና ኮንግረሱን የተማጸኑት ከፍተኛ የጦር መሳርያዎችን ለሀገራቸው እንዲሰጥ ነው ተብሏል፡፡
ከሩስያ ጋር እያደረግነው ያለነው ጦርነት ለኛ ብቻ አይደለም፣ እኛን ለመሳሰሉ ሀገራት ጭምር ነው ሲሉም ተናግረዋል ኦሌና፡፡
አሜሪካ ጦርነቱ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ እጅግ ዘመናዊ የተባሉ የጦር መሳርያዎችን ወደ ዩክሬን መላኳን የተናገሩት ቀዳማዊት እመቤቷ፣ አሁንም ተጨማሪ መሳርያ ያስፍልገናል ብለዋል፡፡
ከሩስያ ጋር በቀላሉ መዋጋት የሚቻል አይደለም፣ በመሆኑም በፍጥነት እርዳታችሁ ያስፈልገናለ ሲሉ ጥሪያቸውን አቀርበዋል፡፡
ኦላና ይህንን የተናገሩት በዋሽንግተን ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ላይ ነው፡፡
ቀዳማዊት እመቤቷ በተደጋጋሚ የጦር መሳርያ የጦር መሳርያ ሲሉ ጥሪያቸውን ለኮንግረሱ አሰምተዋል፡፡
የዩክሬን ቀዳማዊት እመቤት ከዚህ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ስለጦርነቱ ተጠይቀዉ በዚህ ምድር ላይ ባሌን ከኔ የሚነጥቀኝ ማንም የለም ጦርነትም ቢሆን ሲሉ ተናግረው ነበር፡፡
አሁን ጦርነቱ እቤታቸው የደረሰ የመሰላቸው ቀዳማዊት እመቤቷ የድረሱልን ጥሪያቸውን እያሰሙ እንደሚገኙ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም











