ኬንያ ወደ ሶማሊያ በድጋሚ ጫት መላክ ጀምራለች፡፡

የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የሶማሊያዉ አቻቸዉ ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በጋራ ምክክር ካካሄዱ በኋላ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉ ድንበር ክፍት እንዲሆን ተስማምተዋል፡፡
በዚህም የንግድ ዝዉዉሩ እንዲፋጠን ባደረጉት ስምምነት መሰረት ኬንያ በድጋሚ ወደ ሶማሊያ የጫት ምርት መላክ ጀምራለች፡፡

የኬንያዉ ግብርና ሚኒስቴር በትናንትናዉ ዕለት ጫት የጫነ የጭነት አዉሮፕላን ወደ ሞቃዲሾ መብረሩን ገልጸዋል፡፡

ሶማሊያ በፈረንጆቹ 2020 ከኬንያ ጋር በተፈጠረ የባህር ድንበር ዉዝግብ ምክንያት ከኬንያ ምንም አይነት የጫት ምርት ወደ ሀገሯ እንዳይገባ ዕገዳ ጥላ ነበር ፡፡

ከሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ድጋሚ ወደ ስልጣን መምጣት በኋላ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉ ግንኙነት እየተሻሻለ የመጣ ሲሆን፣ የሀገራቱ ነባራዊ ሁኔታም ሰላማዊ እና የረገበ እንደሆነ ሲጂቲኤን አፍሪካ ነዉ የዘገበዉ፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *