የተሰረዘው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ይወጣል ተባለ፡፡

ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በይፋ ዕጣ ከወጣበት በኋል የማጭበርበር ከባድ የሙስና ወንጀል ተፈጽሞበታል ተብሎ፣ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ የተደረገው የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ እንደሚወጣ ተገልጧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙኃን እንዳስታወቁት፣ ትክክለኛ ቀኑን እርግጠኛ ሆኖ መናገር ባይቻልም፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ይወጣል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ በቅርብ ለማውጣት ሌላ ሶፍትዌር እንደሚጠቀሙና፣ ጥራቱ መረጋገጥ እንዳለበት ጠቁመው፣ ትንሽ መታገስ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።

ቤቱን የሚጠባበቀው ሕዝብ ለጥራት ቅድሚያ እንዲሰጥና አስተዳደሩም በጥራት ለመሥራት የሚችለውን ሁሉ ጥረትና ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ጠይቀዋል።

ከንቲባዋ ወ/ሮ አዳነች በድርጊቱ የተጠረጠሩ 16 የሚደርሱ የአስተዳደሩ ሠራተኞችም በሕግ ቁጥጥር ሥር መሆናቸውንና ሌላም የሚመለከተው ሰው ካለም ሕግ የማስከበር ዕርምጃው ይቀጥላል፤›› ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊን
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.