ያለኝ የደም ክምችት ለአምስት ቀናት ብቻ የሚሆን ነዉ—የኢትዮጵያ ደምና ቲሹ ባንክ አገልግሎት፡፡

በአሁኑ ሰዓት በቀን ከ250 ዩኒት አስከ 300 ዩኒት ደም እየተሰበሰበ መሆኑን የኢትዮጲያ ደም እና ቲሹበ ባንክ ተናግሯል፡፡

ጊዜው የክረምት ወቅት እንደመሆኑ የደም መለገስ ተግባሩ በከፍተኛ ሁኔታ መቀዛቀዙን ነግሮናል፡፡

የዛሬ አመት በህግ ማስከበር ዘመቻው የነበረው አይነት መነቃቃት ዓለመኖሩ የኢትዮጵያ ደም እና ቲሹ ባንክ ም/ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሃብታሙ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም በቀን ከ250 ዩኒት ደም እስከ 300 ዩኒት ደም እየተሰበሰበ ቢሆንም ወደ ክልል ከተሞችና ለመንግስት ሆስፒታሎች በዛው ልክ እየወጣ በመሆኑ ያለው ክምችት አገልግሎት ላይ ቢውል ከ5 በላይ አያገለግልም ነው ያሉት፡፡

የተከሰተዉ እጥረት እንደየ የደም አይነቱ የሚለያይ ቢሆንም ፕላትሌት የተሰኘው የደም አይነት የደም አይነት “O” እና የደም አይነት ‘’- O’’ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል ከነበረው የፆም ወቅት እና የበአል ወቅት በመሆኑ የደም ልገሳ ልምዱ መቀነሱን ከብሄራዊ ደም ባንክ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

አሁን የደም እጥረቱ ያለመሻሻሉን ብሎም ክምችቱ ከ5 ቀን በላይ እንደማያገለግል ሰምተናል፡፡

በደም ባንክ የደም እጥረት ሲያጋጥም በየ ሆስፒታሎች ደግሞ የደም ፍላጎት ስለሚጨምርም በዚህ ፍጥነት አገልግሎት ማግኘት ያለባቸው ታካሚዎች መደራረብን ያመጣል ተብሏል።

ለዚህም ሲባል የደም ልገሳውን ህብረተሰቡ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡ ብሔራዊ የደም ባንክም በተለያዩ ቦታዎች ዘመቻዎችን በማድረግ ድንኳኖችንም በመትከል በጎ ፈቃደኞች ደም እንዲለግሱ የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *