በበጀት ዓመቱ በ4.8 ቢሊየን ብር የሚደርስ የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ ተፈጽሟል፡፡

በ2014 በጀት ዓመት ለፌዴራል ባለበጀት መስርያ ቤቶች እና ለመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች አገልግሎት ግዢ ተፈጽሟል ነው የተባለው፡፡
ለተቋማቶቹ የሚውሉ የጋራ መጠቀሚያ ዕቃዎችን በዓለም አቀፍ ግልፅ ጨረታ ዘዴ ግዥ መፈፀሙን የመንግስት ግዥ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው ሪፖርት ገልጿል፡፡

የተፈጸሙ ዕቃዎች ግዥን በተመለከተ ከ2013- 2015 የሚያገለግሉ የቢሮ ፈርኒቸር እንዲሁም ከ2014-2016 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የ5 ሎት (የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ማሽን ቶነሮች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እንዲሁም ለመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የተሽከርካሪ ጎማ) ዕቃዎች የግዥ ሂደት ተጠናቆ በ4.8 ቢሊዮን ብር ለ46 አሸናፊ ድርጅቶች የአሸናፊነት ደብዳቤ መስጠቱም ተመላክቷከል፡፡

የተፈጸሙ ግዥዎች የገንዘብ መጠን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ42 በመቶ ቅናሽ እንዳሳየም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተጠቁሟል፡፡

በ2013 በጀት ዓመት የስንዴ ግዥዎች፣የኮቪድ መከላከያ መሳሪያዎች፣የኔትወርክ ዕቃዎች እና ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ተሽከርካሪዎች ግዥ መፈጸም ዋነኛ የግዢው ገንዘብ መቀነስ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *