በኢትዮጵያ እስካሁን በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው አለመኖሩን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሀይሉ እንደተናገሩት፣ በሀገራችን በአሁን ወቅት በበሽታው የተያዘ ምንም ሰው የለም ፣ነገርግን የቅኝት እና ምላሽ ስራ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ከውጭ የሚገቡ ሰዎች ላይ ምርመራው እየተካሄደ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በድንበር አከባቢ ባሉ ኬላዎች ላይ ከፍተኛ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም አንስተዋል።
የቅኝት እና ምላሽ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያነሱት ዶክተር መሳይ፣ የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣን “ዓለማቀፍ የጤና ስጋት” ብሎ መፈረጁን ተከትሎ ሁሉም ሰው ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *