የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ምዕራባውያን የፍትህ ተቆርቋሪነት ስብዕና የላቸውም አሉ

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ መግላጫ እየሰጡ ነው።
በመግለጫው ምዕራባውያኑ በተለይም አሜሪካ የፍትህ ተቆርቋሪ ለመምሰል የምታደርገው አካሄድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ምዕራባውያኑ ሶሪያን፣ ኢራቅንና ሊቢያን የመሳሰሉ አገራትን አውድመው ዛሬ ላይ ለዩክሬን ተቆርቋሪ ነን የማለት ስብዕና ሊኖራቸው አይችልም ነው ያሉት።

ለዩክሬን ጦርነት መቀስቀስ የምዕራባውያን እጅ እንዳለበትም ሰርጌ ላቭሮቭ አስታውቀዋል ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን የተሰሳተ መረጃን እያሰራጩ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ እያወዘገቡ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

የዩክሬኑ ጦርነትን ተከትሎ የአለም የምግብ ዋጋ መናሩን ያነሱት ላቭሮቭ ለዚህም ምዕራባውያኑን ተጠያቂ አድርገዋል።

ሩሲያ ዩክሬን ላይ የጀመረቸው ልዩ ኦፕሬሽን ለችግሩ እንደ አንድ ምክንያት ቢጠቀሰም እያበባሱት ያለት ግን እነ አሜሪካ ናቸው ብለዋል።

ላቭሮቭ ለዚህ እንደምክንያት ያነሱት ደግሞ ምዕራባውያን ለዩክሬን እያደረጉት ያለውን ወታደራዊ ድጋፍ ነው።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በትናትናው ዕለት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል ።

በዛሬው ዕለት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በሩሲያ ኢምባሲ ችግኝ ተክለዋል።

በኡኑ ሰዓት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለዲፕለማሲ ማህበረሰብና ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ እየሰጡ ሲሆን ኢትዮ ኤፍ ኤምምመግለጫውን እየተከታተለ ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል።

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *