የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበጀት አመቱ ከ27 ቢሊየን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2014 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንዳስታወቁት በተጠናቀቀው የበጀት አመት 27.5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ተገኝቷል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አጠቃላይ የባንኩ ሀብት 1.2 ትሪሊዮን ብር መድረሱንም ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።

ከስራ ዕድል ፈጣራ አንፃርም አጠቃላይ የባንኩ ሰራተኞች 70 ሺህ መድረሳቸው ተነስቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ወቅት 1 ሺህ 8 መቶ 24 ቅርንጫፎች በመላ አገሪቱ እንዳሉትም የባንኩ ፕሬዘዳንት አቶ አቤ ሳኖ ተናግረዋል።

ባንኩ የ2014 ዓ.ም የስራ አፈጻጸምና የ2015 የበጀት ዕቅድ ላይ ግምገማ ጀምሯል።

በመድረኩ ላይ የባንኩ ስራ አስፈፃሚዎች ጨምሮ የዳይሬክተሮች ቦርድ ተገኝተዋል።

በአባቱ መረቀ

ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *