በሃምሌ ወር ዉስጥ 9 ሰዎች ዉሃ ዉስጥ ህይወታቸዉ አልፎ ተገኝተዋል ተባለ፡፡

ዛሬ ማክሰኞ ከጠዋቱ 1:50 በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አየርጤና ሞቢል አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ዉስጥ እድሜዉ 38 አመት የሆነ ሰዉ ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል ።

በሌላ በኩልም ዛሬ ከቀኑ 5:55 በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አሳማ ግቢ አካባቢ በሚገኝ ወራጅ ወንዝ ውስጥ እድሜዉ 30 ዓመት ሰዉ ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል ።

የኮሚሽን መስሪያ ቤታችን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የሟቾቹን አስከሬን ከወንዝ ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል ።

ስለግለሰቦቹ አሟሟት ፖሊስ እያጣራ በአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን በሀምሌ ወር በተለያዩ ምክንያቶች ወንዝ ዉስጥ ሞተዉ የተገኙ ሰዎች ቁጥር 9 ሆኖ ተመዝግቧል ሲል የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል።

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *