በአዲስ አበባ ችግር ያለባቸው የህንፃ ውስጥ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን መለየቱን የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት በማዕከልና በክፍለ ከተማ ከ2 ሺህ 600 በላይ ህንጻዎች የህንጻ ውስጥ የመኪና ማቆሚያ ቦታ አጠቃቀምን ምን እንደሚመስል ገምግሟል፡፡

በዚህም በማዕከል ብቻ በ2 መቶ 60 ህንጻዎች ላይ የህንጻ ውስጥ የመኪና ማቆሚያ ቦታ አጠቃቀም ምልከታ ተደርጓል፡፡

ከነዚህ መካከል 58 ህንጻዎች የመኪና ማቆሚያን በከፊል ለሌላ አገልግሎት ላይ ውለው የተገኙ ሲሆን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ 35 የሚሆኑ ህንጻዎች ማስተካከያ ማድረግ ችለዋል ሲል ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

ሆኖም ቀሪ 23 ህናጻዎች በጊዜ ገደቡ ማስተካከል ባለመቻላቸው እርምጃ እንዲወሰድባቸው እና የንግድ ፈቃዳቸው እንዲታገድ ለሚመለከተው ቢሮ ተልኳል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት መረጃውን ለኢትዮ ኤፍኤም አጋርቷል፡፡

በየዉልሰዉ ገዝሙ
ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *