እህል ጭና ከዩክሬን የተነሳቸዉ የረዞኒ መርከብ ጉዞ ተስተጓጎለ::

ከዩክሬኗ ኦዴሳ ወደብ ወደ ሊባኖስ በትናትናዉ እለት ጉዞ የጀመረችዉ መርከቧ በአየር መዛባት ምክንያት መዘግየቷ ተነግሯል፡፡

ራዞኒ መርከብ 26 ሺህ ቶን በቆሎ ጭና ወደ ሊባኖስ ጉዞ መጀመሯ ይታወሳል፡፡
በጥቁር ባህር ላይ ያለዉ ከባድ የአየር ሁኔታ የመርከቧን ጉዞ እንዳስተጓጎለዉ ዩሮ ኒዉስ ዘግቧል፡:

የቱርክ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት መርከቧ ነገ ጠዋት ኢስታንቡል ትደርሳለች ተብሏል፡፡

የመርከቧ ጉዞ መጀመር በዩክሬን ጦርነት ምክንያት የናረዉን የአለም የምግብ ዋጋ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ያረጋገዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
በቀጣይ ሌሎች የእህል ጫኝ መርከቦች ከዩክሬን እንደሚነሱም ይጠበቃል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *