ኬንያ በአራት ቀናት ብቻ ወደ ሶማሊያ ከላከችዉ ጫት 1.85 ሚሊዮን ዶላር አገኘች፡፡

ኬንያ ከሶማሊያ ጋር የሚያገናገናትን ድንበር እንደገና መክፈቷን ተከትሎ በ አራት ቀን ዉስጥ ወደ ሞቃዲሾ የላከችዉ ጫት ከ1.85 ሚሊዮን ዶላር በላይ አስገኝቶላታል፡፡
የአገሪቱ የኢንዱስትሪ ምርቶች ሃላፊ ፌሊክስ ሙትዊሪ እንዳሉት እስካሁን 84.1 ቶን ወደ ዉጭ ሀገራት መላኩንና በቀጣይ ቀናትም ምርቱ እንደሚጨምር ለኬንያ ኔሽን ሚዲያ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የሶማሊያዉ አቻቸዉ ሃሰን ሼክ ሙሃመድ የሁለቱን ሃገራት ድንበር ዳግም ለመክፈትና የንግድ ልዉዉጥን ለማሳደግ ከተስማሙ ከአንድ ሳምንት ቡሃላ የጫት ግብይቱ መጀመሩን ኔሽን ዘግቧል፡፡

ኔሽን በዘገባዉ በአሁኑ ወቅት ወደ ሶማሊያ የሚሄደዉ አንድ ኪሎ ግራም ጫት በ23 ዶላር ሲሆን በ 2020 ይሰበሰብ ከነበረዉ ያነሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሶማሊያ ከኬንያ ጋር በገባችዉ የባህር ድንበር ዉዝግብ ምክንያት በ2020 በኬንያ ጫት ላይ እገዳ መጠሏ ይታወሳል፡፡

የፕሬዝዳንት ማህሙድ ወደስልጣን መመለስ እና የሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ናይሮቢን መጎብኛታቸዉ ግንኙነታቸዉ ወደ መደበኛ እንዲመለስ ያመቻቸ መሆኑ እየተነገረ ነዉ፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *