ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫም አፈጉባኤዋ በቻይና አካል ወደሆነችው ታይዋን ጉብኝት ማድረጋቸውን ለቻይና ክብር አለመስጠታቸው ማሳያ ነው ሲል አስታውቋል፡፡
ለቻይና ተገንጣይ ቡድኖች እውቅና መስጠት ነው ሲልም ወቅሷል፡፡
ይህ አካሄድ ተገቢ አለመሆኑን ያስታወቀው ሚኒስቴሩ በናንሲ ፔሎሲ ውሳኔ ማዘኑንም አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ለሃገሪቱ ሉአላዊነት እና ብሄራዊ ደህንነትን ለማስጠበቅ ሲባል አስፈላጊውን እርምጃም እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡
በተጨማሪም ለሚመጣው መዘዝ ሁሉ አሜሪካ እና ታይዋን ሃላፊነቱን ይወስዳሉ ሲልም መግለጫውን አጠቃሏል፡፡











