የአሜሪካ ኮንግረስ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ለማረፍ መቃረባቸውን ተከትሎ ቻይና አካባቢውን ለሲቪል በረራዎች ዝግ አድርጋለች፡፡

የናንሲ ወደ ታይዋን ማምራት በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ያነገሰ ሲሆን ታይዋንም የህግ ስርአቷን ጠበቅ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡

ናንሲ ፔሎሲ የሚገኙበት አውሮፕላን በታይዋን የጦር ጀቶች ከመታጀባቸው ባሻገር፣ የአሜሪካ 4 የባህር ሃይል መርከቦች ማምራታቸውን የአሜሪካው መከላከያ መስሪያ ቤት ፔንታጎን አስታውቋል፡፡

የቻይና የጦር ጀቶች በተደጋጋሚ የታይዋንን የአየር ክልል ሲጥሱ መዋላቸውን ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.