የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በጠቅላይ ሚኒስቴሩ የተቋቋመው የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ ላይ ቅሬታ አለኝ ብሏል።

በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፈቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀፅ 63 መሠረት የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ መቋቋሙ ይታወቃል።
በዚህ ቦርድ መቋቋም የታየውን የአካታችነት እና እኩልነት መርህ ጥሰት እንደሚቃወም ማህበሩ ገልጿል።

የማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ሌንሳ ቢዬና፣ የሀገሪቱን ከግማሽ በላይ የሆነውን ህብረተሰብ የሚሸፍኑትን ሴቶች እንዲህ ባሉት ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ አለማድረግ፣ ለተያዙ ጉዳዮች ሙሉ የሆነ መፍትሄ እና ውጤት አያመጣም ብለዋል።
የጥብቅና ሙያ በሁለቱም ፆታ የሚሰራ ስራ መሆኑን ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፣ ቦርዱ ከተሰጠው ስልጣንና ሀላፊነት አንፃር በዘርፉ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊፈጥር የሚችል አካል በመሆኑ ሴቶችን ፈፅሞ አካታች አለማድረጉ በእጅጉ የሚያሳዝን ነው ብለውታል።

ማህበሩ ያለውን ቅሬታ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት፣ለፍትህ ሚኒስቴር ፣ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ አቤት፣ለፌደራል ጠበቆች ማህበር እንዲሁም ሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረቡን አስታዉቋል።

በእስከዳር ግርማ እና ቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.