የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል በውሃ እጥረት ምክንያት የወሊድ አገልግሎት መስጠት አቆመ፡፡

በጎንደር ሆስፒታል የተከሰተውን የውሃ እጥርት አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት ላይ እጅግ መበርታቱ ነው የተገለጸው፡፡
በከተማው የተስተዋለው የውሃ እጥረት በዩኒቨርስቲው የሚተዳደረውን ሆስፒታል እጅግ እየፈተነው ይገኛል ተብሏል፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ የጎንደር ከተማ ነዋሪ የውሃ አቅርቦት የሚያገኝው በወር አንደ ቀን ብቻ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

የጎንደር ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ ዘወዱ ማለደ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ የከተማው ህዝብ ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የውሃ ችግር በከተማው እየተስተዋለ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ የከተማው የውሃ አቅርቦት 18 ከመቶ ብቻ መሆኑን የተናገሩት አቶ ዘውዱ፣ ይሕም ከፍተኛ የውሃ እጥርት ካለባቸው ከቶሞች መካከል እንድትገኝ አድርጓታል ብለዋል፡፡

ከ1930 አመተ ምህረት ጀምሮ በመስመር ውሃ የምታገኝው ታሪካዊቷ ከተማ ጎንደር እስካሁን በከተማው እየተሰራጨ የሚገኝው የውሃ መጠን 13ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በጎንደር ከተማ ከ750ሺህ በላይ ነዋሪዎች መኖራቸውን ተናገሩት ከንቲባው ከጦርነቱ በላይ በውሀ ጥም እየተሰቃዩ ናቸው ብለዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *