ሶማሊያ የቀድሞ የአልሸባብ ቃል አቀባይን የሀይማኖት ሚኒስትር አድርጋ ሾመች፡፡

አዲሱ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር የቀድሞው የአልሸባብ ቃል አቃባይ የሀይማኖት ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀማዝ አብዲ ባሪ የሀገራቸውን አዲስ የካቢኔ ውስጥ የቀድሞ የአልሸባብ ቃል አቀባይ ማካተታቸው ተሰምቷል፡፡

የአልሸባብ የቀድሞ ቃል አቀባይ የነበረው ሙክታር ሮቦው በፈረንጆቹ 2013 ላይ ነበር ከአልሸባብ ጋር ሙሉ በሙሉ የተለያየው አሁን ላይ ግን በሚኒስትርነት ተሾመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀማዝ አብዲ ባሪ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልእክት በሀገራቸው የተንሰራፋውን የሀይማኖት እና የጎሳ ግጭት ከስሩ ለመፍታት ሙክታር ሮቦው ሁነኛ ሰው መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሶማሊያን ካቆሰሏት ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአልሸባብ መሪ በሶማሊያ ስልጣን ማግኝቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል፡፡
አልሸባብ አሁን ላይ ከሶማያ አልፎ ጎረቤት ሀገራትንም ጭምር እያመሰ ይገኛል፡፡

በዚህም ቡድኑ አሁንም ለሶማሊያ እንዲሁም ለጎረቤት ሀገራት የእግር እሳት እየሆነ ይገኛል፡፡
ይህ በሆነበት ሁኔታ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀማዝ የቡድኑን ቀንደኛ ሰው የሀይማኖት ሚኒስትር አድገው የሾሙት፡፡

አልጀዚራ

በሄኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *