የዩክሬን እህል ጫኝ መርከብ ራዞኒ ኢስታንቡል ደርሳለች፡፡ By ethiofmAdminAugust 3, 2022August 3, 2022የውጭ ዜና የሴራሊዮን ባንዲራ ያነገበችዉ የዩክሬን እህል ጫኝ መርከብ ራዞኒ ኢስታንቡል መድረሷ ታዉቋል፡፡ 186 ሜትር ርዝመት ያላት መርከቧ ከኦዴሳ ወደብ ሰኞ ዕለት ነበር 26 ሺህ ቶን በቆሎ ይዛ የተንቀሳቀሰችዉ፡፡ መርከቧ ሁለተኛ ጉዞዋን ወደ ሊባኖስ ከማድረጓ በፊት በቱርክ አለምአቀፍ አባላት ባሉት ቡድን ፍተሻ እንደሚደረግላት ሩፕትሊ ኒዉስ ነዉ የዘገበዉ፡፡