የቡርኪናፋሶ ጦር ሰላማዊ ሰዎችን መግደሉን አመነ::

የቡርኪናፋሶ ጦር በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በሀገሪቱ ደቡብ ምስራቅ ባደረገው ወታደራዊ ዘመቻ ሰላማዊ ዜጎችን መገደላቸውን አምኗል፡፡

የምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር በአማፂ ቡድኖች፣ አንዳንዶቹ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጨምሮ በተደጋጋሚ ጥቃቶች ሲፈፅሙ በነበሩት ላይ እርምጃ ወስዶ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም “በመቶዎች የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን መደምሰሱን አስታውቆ በሚያሳዝን ሁኔታ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ መጥፎ አጋጣሚ ነው ” ሲል የሰራዊቱ መሪ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ምን ያህል ሰላማዊ ዜጎች እንደተገደሉ ግን እስካሁን የሚያሳዩ መረጃዎች አለመኖራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *