የቻይና ጦር ቃሉን እንደሚጠብቅ አስታወቀ::

የቻይና ብሄራዊ መከላከያ ሚኒስተር ታን ኬፊ ጦሩ ቃሉን እንደሚጠብቅ አስታዉቀዋል፡፡
መከላከያ ሚኒስተሩ በሰጡት መግለጫ በታይዋን ደሴት ዙሪያ የሚደረጉ ወታደራዊ ልምምዶች በአሜሪካ እና በታይዋን መካከል ያለዉ የሚስጥር ስምምነት ላይ አደጋ ይጥላል ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ኮንግረንስ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን መጎብኘት አሜሪካ የታይዋን ነጻነትን በመቃዎም የገባችዉን ቃል ከድቶ የቻይናና የአሜሪካን ግንኙነት በእጅጉ እንደሚጎዳም ተናግረዋል፡፡

ታን የአሜሪካና ተግባር በታይዋን ክልል ላይ አደጋ ከማምጣቱም በላይ ለህዝቡም አሳሳቢ ስለመሆኑ አስታዉቀዋል፡፡
ቻይና ብሄራዊ ሉአላዊነቷን እና የግዛት አንድነቷን ትጠብቃለች፤ ለማንኛዉም የታይዋን ነጻነት ዕርምጃ ወይም የዉጭ ጣልቃ ገብነት ምህረት እንደሌለዉም አስምረዉበታል፡፡

ቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.