የቱርኩ ፕሬዝዳንት በድጋሜ ፑቲንን ሊያገኙ ነው::

የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲጵ ጣይጵ ኤርዶሃን በዛሬው ዕለት ወደ ሩሲያዋ ሶቺ በማቅናት ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር እንደሚገናኙ ተነግሯል።

የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት በሁለትዮሽና በ አለም አቀፋ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ያለመ ስለመሆኑም ታውቋል።

ከሰሞኑ በቱርክ አደራዳሪነት የዪክሬን እህል ጫኝ መርከብ እንድትንቀሳቀስ ከተደረገ በኋላ ነው ኤርዶሃን ወደ ሶቺ የሚያቀኑት።
ኤርዶሃን ሩሲያን ሲጎበኙ በሶስት አመታት ውስጥ ያሁኑ ለ8ኛ ጊዜ ነው።

ከሳምንት በፊት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን ከኢራኑ አቻቸው ኢብራሂም ሬይሲና ከቱርኩ ኤርዶሃን ጋር ቴህራን ውስጥ በገናኘታቸው ይታወሳል።

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *