በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎችና ልዩ ልዩ ንብረቶች 45.8 ሚሊየን ብር ገቢ መገኘቱን የመንግስት ግዥ አገልግሎት አስታወቀ።

አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ የ21 ፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች 53 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በሽያጭ በማስወገድ 27 ሚሊዮን 904 ሺህ 518 ብር እንዲሁም የ28 ተቋማት 94 ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን በሽያጭ በማስወገድ 17 ሚሊዮን 873 ሺህ 554 ብር ማግኘቱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

በድምሩም በበጀት ዓመቱ ዉስጥ ተሽከርካሪዎችንና የተለያዩ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ ሽያጭ በማስወገድ 46 ሚሊዮን ብር አካባቢ ገቢ ተገኝቷል ብሏል፡፡

በሽያጭ ሂደቱ የተገኘው ገቢ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ26.7 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱ ነው የተገለፀው፡፡

ለዚህም ዋነኛው ምክንያት በአገልግሎቱ በኩል ለማስወገድ ለ3ኛ ጊዜ ለጨረታ ከቀረቡት 137 ሎት ንብረቶች 123 ሎት በተጫራቾች ዋጋ ሳይቀርብባቸው ቀርቶ ሳይወገዱ መቅረታቸው አንዱ መሆኑ ተጠቁማል፡፡

ሌላናው እና ዋናው ምክንያት ደግሞ በአገልግሎቱ በኩል የሚወገዱ ንብረቶች የዋጋ ግምት የገንዘብ ጣሪያ ከነበረበት 100 ሽህ ብር ወደ 500 ሽህ ብር በላይ ከፍ በመደረጉ በመ/ቤቶች የሚቀርበው የንብረት ይወገድልን ጥያቄ በመቀነሱ እንደሆነ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ገልጿል።

በረድኤት ገበየሁ

ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.