ደቡብ ኮሪያ የመጀመሪያ የጨረቃ ምህዋሯን አስወነጨፈች፡፡

ደቡብ ኮሪያ በኤሎን መስክ የኤሮስፔስ ኩባንያ በሆነዉ ስፔስ ኤክስ የመጀመሪያዉን የጨረቃ ምህዋር በመላክ በጨረቃ ላይ የሚደረገዉን ዉድድር ተቀለቅላለች፡፡

ከፍሎሪዳ ኬፕ ካናቨራል የተነሳችዉ ‹‹ዳኑሪ ››የተሰኘችዉ የጨረቃ ምህዋር ዘጠኝ ፋልኮን ሮኬቶችን ተሸክማ ታህሳስ ወር ላይ ወደ ጠፈር ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሊሳንግ ሮያል የኮሪያ ኤሮስፔስ ጥናት ኢኒስቲትዩት ፕሬዝዳንት ይህ በኮሪያ የጠፈር ምርምር ታሪክ ዉስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠዉ ክስተት ነዉ ብለዋል፡፡

ለመገንባት ሰባት አመታትን የፈጀችዉ‹‹ ዳኑሪ›› ሳተላይቶችን ወይም የጠፈር መንኮራኩሮችን ለማገናኘት የገመድ አልባ የኢንተርኔት ምህዳር ለመዘርጋት እንደምትረዳም ነዉ የገለጹት፡፡

ዳኑሪ ለአንድ አመት በምታደርገዉ ተልእኮ ዉስጥ ለቀጣይ ተልእኮዎች ማረፊያ ቦታዎችን ለመለየት ብሎም የጨረቃን ወለል ለመመርመር የሚያስችሉ ስድስት የተለያዩ መሳሪያዎችን እንደምትጠቀም ተነግሯል፡፡

ከመሳሪያዎቹ አንዱ ረብሻን የሚቋቋም በአዉታረ መረብ ላይ የተመሰረቱ የጠፈር ግንኙነቶችን መገምገም መቻሉ በአለም የመጀመሪያዉ እንደሚያስብለዉ የደቡብ ኮሪያ ሳይንስ ሚኒስትር መግለጹን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *