በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል በጋዛ ሰርጥ በተነሳው ግጭት 41 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።
እስራኤል ባለፈው አርብ ጂሃዲስቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው በሚል በጋዛ ተኩስ መክፈቷ የሚታወስ ነው።
ይህም ጥቃት እስራኤልና ፍልስጤም ባለፈው አመት ካደረጉት የ 11 ቀን ጦርነት በኋላ የተካሄደ ከፍተኛው ግጭት ተብሎለታል።
በአሁኑ ግጭት የ41 ሰዎች ህይዎት እንዳለፈ የዘገበው ሲጂቲኤን በግብፅ አደራዳሪነት ሁለቱ ወገኖች የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል።
እስራኤልና ፍልስጤም በጋዛ ሰርጥ በሚያደርጉት ተደጋጋሚ ግጭት የበርካታ ዜጎችን ህይወት መቅጠፉ እንደቀጠለ ነው።
በአባቱ መረቀ
ነሃሴ 02 ቀን 2014 ዓ.ም











